
የኤጀንሲው የማኔጅመንት አባላት በየካ ክ/ከተማ የመስክ ምልከታ አደረጉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታችዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የማኔጅመንት አባላት በ10/08/2016 ዓ/ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 እና 9 የመስክ ምልከታ አከናውነዋል፡፡
በመስክ ጉብኝቱ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በቆዳና በቆዳ ውጤቶች ምርት ክላስተር የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ የግቢያቸው የጥበቃና ፅዳት ሁኔታ፣ ያሉ ተግዳሮቶችና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴያቸው ላይ ምልከታ ተደርጓል፡፡
በሌላም በኩል ወረዳ 9 መብራት ኃይል የሚገኙና በልማት ምክንያት እየተነሱ ያሉ የመስሪያ ቦታዎች አጠቃላይ ሁኔታ መመልከት ተችሏል፡፡
የማኔጅመንት አባላቱን የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የጊቢ ማስዋብና ጽዳት፣ ያለስራ የተቀመጡና የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ያለባቸውና ለልማት ተነሺዎች ምትክ የመስሪያ ቦታዎች የማልማት ሂደት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.