
የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ሾላ የተባበሩት አምራች ማህበር ላይ ጉብኝት አካሂዷል።
በጉብኝቱም የኤጀንሲው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የክ/ከተማ የመዋቅሩ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች እና የመስሪያ ቦታዎች ግቢ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ተሳትፈዋል።
ጉብኝቱ በዋናነት በመስሪያ ቦታዎች ተረፈ ምርት አጠቃቀም፣ በገበያ ትስስር፣ በክላስተር ፅንሰ-ሀሳብ እና በመስሪያ ቦታዎች ምቹነት ላይ ያተኮረ ነው።
በጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተርና የመስሪያ ቦታ ልማትና ማስተላለፍ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ የጉብኝቱ ዋና አላማ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በመውሰድ በሌሎች የመስሪያ ቦታዎችና በቀጣይም በሚገነቡ የመስሪያ ቦታዎች ላይ ለመተግበር እንደሆነ ገልፀዋል።
የኤጀንሲው ዋና አላማ የመስሪያ ቦታዎችን ማስገንባትና ማስተላለፍ እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ ሰብለወርቅ በጉብኝቱ የተሳተፉ አካላት ያገኙትን ምርጥ ተሞክሮ በሌሎች መስሪያ ቦታዎች ላይ መተግበር እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ወ/ሮ ሰብለወርቅ አክለውም ጉብኝቱ በቀጣይ ተገንብተው የሚተላፉ መስሪያ ቦታዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.