
የአዲስ አበባ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የ9 ወር አፈፃፀሙን ከመዋቅሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ገመገመ፡፡
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተርና የመስሪያ ቦታ ልማትና ማስተላለፍ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ኤጀንሲው በ9 ወሩ በርካታ አዎንታዊ ተግባራትን ማከናወን ቢችልም አፈፃፀማችን የተለያየ በመሆኑ ወጥነት ያለው እንዲሆን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
አክለውም ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ በቅንጅታዊ አሰራሮች በመታገዝ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ቅድሚያ ሰጥተን እንሰራለን ያሉ ሲሆን የተዘጋጁ ደንብና መመሪያዎች ሲፀድቁ ተመሳሳይ አረዳድ እንዲኖር የሚረዳ የዓቅም ግንባታ ስልጠናም ይሰጣል ብለዋል፡፡
የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተርና የአስተዳደርና ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መርቆ ብርሌው በበኩላቸው በቀጣይ ክፍተትን የለየ ክትትልና ድጋፍ በአመራሩና በባለሙያዎች በማድረግ ተግባራት አሰራራቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጡት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ከሪፎርሙ ጎን ለጎን የተከናወነው የ9 ወር የተግባር አፈፃፀም የተሻለ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለህብረተሰባችን የገባነውን ቃል እውን ሊያደርግ የሚችልና በሁልም ደረጃ ተቀራራቢነት ያለው ተግባር ማከናወን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.