
የመጀመሪያ ቀን
icon
የመጨረሻ ቀን
icon
አካባቢ
የአዲስ አበባ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ
በኤጀንሲው በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት የሚከናወነው የሰራተኞች ማነቃቂያ መድረክ ዛሬም ተከናውኗል፡፡
(12/09/2016 ዓ/ም) የዛሬውን የህይወት ተሞክሮ ያቀረቡት የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኢጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተርና የመስሪያ ቦታዎች ልማትና ማስተላፍ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ሲሆኑ በመድረኩም የምናከናውናቸው ተግባራት በቅንጅት ካልተከናወኑ በስተቀር በተናጠል ሩጫ ውጤታማ መሆን አይችሉም ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ዛሬ ላይ ያሉበትን ደረጃ ለመድረስ ያለፉባቸውን የህይወት ውጣ ውረዶችና ስኬቶች በተሞክሮነት ለተሳታፊዎች ግልፅ በሆነ መንገድ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በየሳምንቱ የተጀመረው የእርስ በርስ የመማማሪያና የማነቃቂያ መድረክ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አውስተው ሁላችንም እድሉን አግኝተን አንዳችን ከአንዳችን እየተማማርንና ልምድ እየተለዋወጥን ለላቀ ውጤት በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
መረጃው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
"