የዜጎች ስምምነት ቻርተር ሰነድ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡
ስለሆነም ኤጀንሲው የሚሰጠው አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩን የመስሪያ ቦታ የማልማት አቅምና የተገልጋይ ፍላጎትን መሰረት የመስሪያ ቦታ አቅርቦት በፍትሀዊነት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የኤጀንሲው አመራሮችና ሠራተኞች ሊተገብሩትና ሊከተሉት የሚገባ ይህ የዜጎች ስምምነት ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡