የመስሪያ ቦታዎች አስተዳደርና ቁጥጥር ዘርፍ
ምክትል ቢሮ ኃላፊ:
አቶ መርቆ ብርሌው

1. በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ወይም የሚዘጋጁ የመስሪያ ቦታዎችን ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤ 2. የመስሪያ ቦታ አሰጣጥ እና ማስተላለፍ የአሰራር ሥርዓት ጥናት ያቀርባል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 3. ዕድሳት እና ጥገና የሚያስፈልጋቸው መስሪያ ቦታዎችን በጥናት በመለየት የእድሳት እና የጥገና ስራ ያከናውናል፤ 4. በህገ-ወጥ መንገድ የማምረቻ፣ ማሳያና መሸጫ ማዕከላት ተላልፈው ሲገኙ የተላለፈላቸውንም ሆነ የሚያስተላልፉ አካላት ላይ ክትትል ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 5. የመስሪያ ቦታዎች ሲተላለፉ ተጠቃሚዎች ከተዋዋሉበት የስራ ዘርፍ አላማና ተግባር ውጪ እንዳያውሉ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ አውለው ሲገኙም የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ 6. በመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ይለያል፤ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል፤ ውጤቱንም ተግባር ላይ ያውላል፤ 7. የክላስተር ማዕከላት ልማት ከኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እና ወቅታዊ መሆኑን በየጊዜው ያረጋግጣል፤ እንደአስፈላጊነቱ በመፈተሽ እንዲስተካከል የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ ተግባር ላይ ያውላል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 8. በመስሪያ ቦታ ውስጥ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች በመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ተግባራት ላይ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ያደራጃል፤ 9. ለሚያደራጃቸው ኮሚቴዎች መተዳደሪያ ደንብ ያወጣል፤የአፈፃፀም ማኑዋል ያዘጋጃል፤ተግባርና ኃላፊነታቸውን በማሳወቅ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
በዘርፉ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች:
ምንም አልተገኘም.